የፓይሰስ ተስማሚ የስራ መስክ

የፓይሰስ ተስማሚ የስራ መስክ The dreamer, imaginative »» ፓይሰሶች የዞዳይኩ ህልመኞች ናቸው፣ መቼም ቢሆን ማለምን አያቆሙም፣ ስለወደፊቱም ሆነ ስለ ማንኛውም ነገር በአይነህሊናውቸው ይስላሉ፣ ብዙዎች ራሳቸውን update እንዳልሆኑ አይነት ስሜት ይሰማቸዋል፣ ነገር ግን ጥሩ የፈጠራ ተነሳሽነት አላቸው። »» ባህላዊ ነገሮች ላይ ጥሩ ናቸው፣ ሩህሩና ነገሮችንም በአስተዋይነት ስለሚያዩ፣ ፈጠራ የሚጠይቁ ስራዎች ላይ ጎበዝ ናቸው፣ ነገር ግን አደባባይ ላይ፣ በግንዘብ የተጠላለፈና ትልቅ ትኩረት የበዛበት ስራ ባይሰሩ ይመረጣል። ጠንቃቃ ናቸው፣ ነገር ግን የሆነ ግዜ በሀሳብ እልም ሊሉ ይችላሉ። »» የእንቅልፍ ስራአታቸው፣ ሊለወዎጡ ስለሚችሉ፣ ቤት ውስጥ በነፃነት የሚሰሩ ስራዎች የበለጠ ያነሳሷቸዋል። ፓይሰሶች ውስጣዊ ጥንካሬና ውዥንብር ስላለባቸው ትክክለኛ ፍላጎታቸውንና አውነተኛ አላማቸውን ከሰው ለመሰወር ይገደዳሉ። በስራቸው ከተደሰቱ በደንብ ይሰራሉ፣ ካልሆነ ግን አልምጥ ነው የሚሆኑት። ቶሎ መከፋታቸውን ለመቆጣጠር ከቻሉ፣ አንፀባራቂ ነገር ማምጣት ይችላሉ። በጣም ስሜተ ስስ ስለ ሆኑ ። √√ ጥሩ እሴቶች »» ሩህሩህ፣ አስተዋይ፣ ተስማሚ፣ ስሜታዊ፣ ባለ ረዕይና ሀሳባዊ ናቸው፣ በሀሳብ የሚያስቡትንም ነገር ተግባራዊ ማድረግ ይችላሉ። √√ ስኬታማ የስራ መስክ »» አርቲስት፣ ሳይኮሎጂስት፣ ሆስተስ፣ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ውስጥ፣ ነርስ፣ ቴራፒስት፣ ፎቶግራፈር፣ ፊልም ሜከር፣ ሙዚቀኛ፣ ሼፍ፣ ኢንጂነሪንግ፣ የማስታወቂያ ባለሞያና የመሳሰሉት። »» √√ ተስማሚ ያልሆኑ መስኮች »» ማንኛውም አይነት ስራ ይሁን፣ ከሰው ጋ የሚያጋጩና የሚያቀያይሙ ከሆነ መቼም አይፈልጉም።
የፓይሰስ ተስማሚ የስራ መስክ Reviewed by nestamereja on 5:37 AM Rating: 5

No comments:

All Rights Reserved by NESTA MEREJA © 2014 - 2015
Powered By Blogger, Share by Star Tuan

please fill the following

Name

Email *

Message *

Theme images by konradlew. Powered by Blogger.