የጄሚኒ ተስማሚ የስራ መስክ

የጄሚኒ ተስማሚ የስራ መስክ The genius, The magic mind »»ጄሚኒን እንደፈለገኝ እናገራለው ማለት ይከብዳል፣ ምክንያቱም እናንተ በተናገራቹት ልክ እነሱ አፀፋውን በእጥፍ ይመልሳሉ፣ ሚሉትን አያጡም። ምጡቅ አዕምሮ አላቸው፣ በጣም ውስብስብና ከባድ ሀሳብን በቀላሉ ማስረዳት ይችላሉ፣ የጄሚኒዎች ገዥ ሜርኩሪ አንደበትን ታዛለች፣ ፈጣን አስተማሪና አስተርጓሚ መሆን ይችላሉ፣ ፕሮፌሽናል ናቸው፣ ንግግርም ላይ እንደዛው። »» ጄሚኒዎችን ደስተኛ ለማድረግ በእውቀት ሚጥለቀልቁበትን ነገር ስጧቸው ወይም አሳዯቸው፣ ነገር ግን ሁለት የተለያየ ባህሪ ስላላቸው፣ ዙሩን ፈጣንና አከባብያዊ ማድረግ አለባቹ፣ አዝጋሚና አሰልቺ ከሆነባቸው ምንም ሳያቅማሙ ይጠፋሉ፣ ወይም ገሸሽ ያደርጉታል። ጉዞ ያለበት ስራና አከባቢያዊ መስተጋብር ያለበት ስራ ይወዳሉ። በጎ አሳቢና በሙሉ ሀይላቸው ይሰራሉ። ባህላዊ ነገሮችን ከመከተል ይልቅ፣ ራሳቸውን ሚገልፁበትን ነገር ይወዳሉ። »» የጄሚኒ ሀሳባዊ ስራቸው፣ ፈጣንና በሚገባ አዕምሯቸውን ማሰራት ሚችሉበት ቢሆን ይመርጣሉ። ነገሮችን በፈጣን ሁኔታ መልመድና መስራት ይችላሉ፣ ነገር ግን ከለመዱት ኅላ ሊያዝጋቸው አይገባም። በብዥታ አለምና በእውነተኛ አለም መካከል ያለውን ልዩነት እንዲያዎቁት ጥረት ማድረግ አለባቸው፣ በሁለት አለማት ድንበር ላይ ከመጥፋት ለመዳን ይጠቅማቸዋል። √√ ጥሩ እሴቶች »» ቀልደኛ፣ፈጣን፣ ጎበዝና ተላማጅ ናቸው፣ ነገር ግን ሀሳባቸውን ብዙ ነገር ላይ መጣዳቸው ድብርት ውስጥና ውጤማ ላያደርጋቸው ስለሚችል፣ አንድ ነገር ላይ ብቻ ትኩረት ቢያደርጉ ምርጥ ነው። √√ ስኬታማ የስራ መስክ »» ሚድያና ማስታወቂያ፣ ማርኬቲንግ፣ ጋዜጠኛ፣ ፀሀፊ፣ የቴሌ ኦፕሬተር፣ ረዳት ቴክኒሺያን፣ አስተማሪ፣ አርክቴክት፣ ማሽን ኦፕሬተር፣ ኮሜዲያን፣ ፖሎቲከኛ፣ ቴክኖሎጂ ላይና የመሳሰሉት ላይ ምርጥ ናቸው። √√ ተስማሚ ያልሆኑ መስኮች »» ጥብቅና ቁጥጥር ያለበት ስራ ሆኖ፣ ስረው ላይ ደግሞ እያንዳንዷን ጥቃቅን ነገር እነሱን ሚጠብቅ አይነት ስራ ከሆነ ቶሎ ላጥ ቢሉ ነው ሚሻላቸው።
የጄሚኒ ተስማሚ የስራ መስክ Reviewed by nestamereja on 5:39 AM Rating: 5

No comments:

All Rights Reserved by NESTA MEREJA © 2014 - 2015
Powered By Blogger, Share by Star Tuan

please fill the following

Name

Email *

Message *

Theme images by konradlew. Powered by Blogger.