የሳጁታሪየስ ተስማሚ የስራ መስክ

የሳጁታሪየስ ተስማሚ የስራ መስክ Searching, the sage »» ሳጁታሪየሶች ነፃነትን አፍቃሪ፣ ከማንኛውም ተፅዕኖ መላቀቅ የሚፈልጉ፣ በሆነ ሳጥን ውስጥ መሆንና ባለፈበት ባህልና ህግ መመራት የሚጠሉ ናቸው። አብረው ከእነሱ ጋር የሚሰሩ ሰዎች እንደ ግሩፕ ብዙ ስኬትን ያስመዘግባሉ፣። በአስተዳደርነት ሆነ በካንፓኒው ባለቤትነት ሚመራው ህግ እያለ ፈታ ያለ የስራ አከባቢ በዙሪያቸው ካለ፣ ፈታ ብለው እየዞሩ ነው መስራትን የሚፈልጉት፣ ከመስሪያ ቤቱ ውጪም ሆነው ሊሆን ይችላል የሚሰሩት። »» ህግ መስበርና አዲስ ነገርን መፍጠር ላይ ጎበዝ ናቸው። ሀቀኛ፣ በሙሉ ሀይላቸው የሚጠቀሙና የራሳቸውን ፍልስፍና የሚከተሉ ናቸው። ውሳኔ ላይም ፈጣን፣ ተራማጅና ትክክለኛ ናቸው። ብዙ አማኝ ሳጁተሪየሶች አሉ፣ ሲበዛም ተጓዥ ናቸው። »» ወጣ ያሉ ሲሆኑ፣ ቀልድም ይወዳሉ፣ ይቀልዳሉም። ጥሩ ተወዳጅነትም አላቸው፣ እየሰሩና እያሳዩ ነው የሚሰሩት። ለእያንዳንዱ ነገር ስለማይጨነቁ፣ ስለወደቀች ቆሻሻና ትናንሽ ነገር ላያስተውሉ ይችላሉ። የተለመደ ነገር መስራት ቶሎ ነው ስልችት ሚላቸው። ሁሌም ለወጥ ያለና እድገት ያለው ፍልስፍና ነው የሚፈልጉት። √√ ጥሩ እሴቶች »» ለየት ያለ ነገር ማምጣት የሚችሉ፣ ተስፈኛ፣ ቀጥተኛና ነፃነታቸውን በእንቅስቃሴና ራሳቸውን በመግለፅ ዘና የሚሉ እንዲሁም ፈልገው የገቡበትንና የሰሩትን ስራ ምርጥ አድርገው መስራት የሚችሉ ናቸው። √√ ስኬታማ የስራ መስክ »» ኢንተርፕሬነርሺፕ ፣ ፓይለት፣ ስፖርት ኢንዱስትሪ፣ ፖሊስ ኦፊሰር፣ ሆስተስ፣ ሚኒስተር፣ የእንስሳት አሰልጣኝ፣ ኤዲተር፣ ህዝብ ግንኙነት፣ አሰልጣኝና ማንኛውንም አይነት ስራ ከጉዞ ጋ በተገናኘ፣ አስተማሪ፣ ዲፕሎማት፣ ፕሮፌሰር፣ ሰባኪ፣ ሪፖርተር፣ ሳይንቲስትና ደላላ መሆን ይችላሉ። √√ ተስማሚ ያልሆኑ መስኮች »» ድግግሞሽ የበዛበት፣ የሙሉ ቀን የቢሮ ውስጥ ወይም የጠረቤዛ ላይ ስራ ።
የሳጁታሪየስ ተስማሚ የስራ መስክ Reviewed by nestamereja on 5:35 AM Rating: 5

No comments:

All Rights Reserved by NESTA MEREJA © 2014 - 2015
Powered By Blogger, Share by Star Tuan

please fill the following

Name

Email *

Message *

Theme images by konradlew. Powered by Blogger.