የካፕሪኮርን ተስማሚ የስራ መስክ

የካፕሪኮርን ተስማሚ የስራ መስክ Corporate, The CEO »» ሁነኛውና የሌላ ኮኮብ ተፅኖ ጎልቶ ማይታይበትን ካፕሪኮርን፣ ማግኘት ከፈለጋቹ፣ በእርግጠኛነት ትልቅ ክብር ያለው ስራ ላይ ወይም ደግሞ ትልቅ ሽልማት ሲጎናፀፉ ተገኛቿላቹ። ካፕሪኮርኖች በሕይወታቸው እንድ ትልቅ ነገር ማግኘት ይፈልጋሉ፣ እሱም ስኬትን። ትልቅ ስኬት ሚገኝበት ስራ ሲያገኙም ትልቅ ሀሴት ነው ሚሰማቸው፣ ያማልላቸዋል። ነገር ግን ስሜታቸውን ያገናዘበ የተወሰነ ፕሮሞሽን ይፈልጋሉ፣ ትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ ፕሮሞሽን። »» ትላልቅ ተልኮና ግብ ተሰቷቸው ሚሰሩትን ስራ ይወዱታልም በአስተማማኝ ሁኔታም ይጨርሱታልም። ለምሳሌ የFBI አለቃ J.edgar hoover አስተማማኝ ምሳሌ ነው። ካፕሪኮርኖች ትልቅ ምኞት አላቸው፣ ደስተኛ መሆንንም ከልብ ይፈልጉታል፣ ገደብ ያላቸውና በአቋማቸው ፅኑ ናቸው፣ የፈለገውን ግዜ ይወሰድ አንዴ ከቆረጡ፣ ቆረጡ ነው። ለመለወጥ ይሰራሉ። »» ሁሉም በህግና ደንብ ቢሆን ይመርጣሉ፣ ህግና ደንብንም የማክበር ዝንባሌ አላቸው። አሪፍ የቢዝነስ ሀሳቦችን መጀመር ላይ ጎበዝ ናቸው። በአከባቢያቸው ያሉትን ሀሳቦችንም ሆነ ሰዎችንም፣ ወደ አንድ ያመጣሉ። √√ ጥሩ እሴቶች »» ጥሩ ምኞት፣ ትልቅ አቅም፣ ታጋሽ፣ በህግ የሚመሩ፣ አካሄድን አዋቂና ተወዳዳሪ አንዲሁም ማንኛውንም ስራ ቢሰጣቸው፣ አሪፍ አድርጎ መስራት ይፈልጋሉ። √√ ስኬታማ የስራ መስክ »» ፋይናንስ ላይ፣ ቢዝነስ አስተዳደር፣ ዶክተር፣ አሰልጣኝ፣ ማናጀር፣ ባንከር፣ የኮምፒተር ባለሙያ፣ ስቶክ ኤክስፐርት፣ ኢንቨስተርና እንዲሁም ጥሩ የፈጠራ ሰው መሆን ይችላሉ። በዛ ላይ ደግሞ ውክልናና ፕላን ላይ ምርጥ ስለሆኑ፣ ሰውን ጥንቅቅ አድርገው ማማከር ስለሚችሉ፣ ኮንሰልታንሲ ላይ አሪፍ ናቸው። √√ ተስማሚ ያልሆኑ መስኮች »» ምንም ጥቅሙ ሳይታወቅ በድፍረት ሚገቡበት ስራም ሆነ ቢዝነስ ብዙ ዋጋ ያስከፍላቸዋል።
የካፕሪኮርን ተስማሚ የስራ መስክ Reviewed by nestamereja on 5:40 AM Rating: 5

No comments:

All Rights Reserved by NESTA MEREJA © 2014 - 2015
Powered By Blogger, Share by Star Tuan

please fill the following

Name

Email *

Message *

Theme images by konradlew. Powered by Blogger.