የአኳሪየስ ተስማሚ የስራ መስክ

የአኳሪየስ ተስማሚ የስራ መስክ Adaptable , The visionary »» አኳሪየሶች የፈለጉትን የእጣ ካርድ ያንሱ፣ ያገኙትን እጣ እንዳለ ወደፈለጉበት መውሰድ ይችላሉ፣ የሁሉም እጣዎች ጆከር ናቸው። በፈለጉት ሞያ ቢገቡ ነጥሮ መውጣት ይችላሉ፣ ከሕይወታቸው ጠንቅቀው ልምድ መውሰድ ይችላሉ። ያገኙትንም እውቀት ምንም ሳይሰስቱ ይሰጣሉ፣ በስራ አካባቢ ላይ በጎ አድራጎት ያበረታታሉ፣ ስለ ፍትህና እኩልነትም ይቆማሉ። »» አዳዲስና ጀብዱ የተሞላበት ነገሮችን ይናፍቃሉ፣ ይወዳሉ እንዲሁም ያልማሉ። በአንድ ወኪል ወይም ማህበር ብቻ መታሰርን ይጠላሉ፣ በዚ አጋጣሚም፣ እድሉን የሚያገኙ ከሆነ ብዙ ስራ ይለዋውጣሉ። ነፃነታቸው ሕይወታቸው ነው፣ ከተለመደ ስራና ነገር ራሳቸውን ማላቀቅ ይፈልጋሉ። ተሞክሮ የማያቅ በማንም ለመስራት የማይገመት ስራ መስራትና መሞክርን ይወዳሉ። »» ኦርጂናል ናቸው ነገር ግን በሁለት ሐሳብ መሀል ሲሆኑ ይስተዋላል፣ የሆነ ግዜ ላይ ሀይለኛ ሀይልና ፍላጎት ከዛን ደግሞ ቀዝቀዝና ድክም ወደ ማለት ይመጣሉ። ይሄም በገዥያቸው ኡራኖስ ምክንያት ይከሰታል። √√ ጥሩ እሴቶች »» ጥሩ ተንታኝ፣ ጎበዝ፣ ፈጠራ ላይ እንዲሁም ጓደኝነትና ከማንም ጋር ተግባብቶ መኖር ይችላሉ፣ ምንም አይነት ሰው ይሁን። √√ ስኬታማ የስራ መስክ »» አፕ ዲቨሎፐር፣ ሳይንቲስት፣ የእንስሳት ሀኪም፣ ኢንጂነር፣ ዲዛይነር፣ ሙዚቀኛ፣ የህዋ ተመራማሪ፣ የነፃነት ተከራካሪ፣ ሶሻል ሚዲያ ላይና የመሳሰሉት ላይ ምርጥ ናቸው። √√ ተስማሚ ያልሆኑ መስኮች »» ምንኛውም አይነት ስራ ይሁን፣ ተለምዷዊ ሆኖ፣ ነፃ ሆኖ ማሰብንም ሆነ ልዩነትን የሚቃወም የስራ ኢንቫይሮመንት ከሆነ ትዕግስት የላቸውም። የካንሰር ተስማሚ የስራ መስክ Caring, the mystic »» ካንሰሮች ስሜታዊ ናቸው፣ እንዲሁም በቀላሉ የሰውን ልብ፣ አዕምሮና ውስጣዊ ፍላጎት መረዳት ይችላሉ። የሕይወት ነገር ለነሱ በጣም ወሳኝ ነው፣ በተለይ ደግሞ ቤተሰብን በተመለከተ፣ እንዴትና ደስተኛ ቤተሰብ መምራት እንዳለባቸው ይጨነቃሉ፣ በዚህ እሳቤም ምን አይነት ስራ ቢሰሩ ውጤታማ መሆን እንዳለባቸው ጠንቅቅው ያውቃሉ፣ ያጤናሉ። »» ምርጥ ሼፍ ናቸው፣ ምግብ ይጣፍጥላቸዋል፣ የአንድ ሬስቶራንት ወይ ሆቴል ማናጀር ቢሆኑ ማንንም ደንበኛ አጠረግርገው መሳብ ይችላሉ፣ በተፈጥሯቸው ተፈጥሮ ነገሮች ይስባቸዋል፣ እንደ ነርሲንግ፣ የህፃነትና የአዛውንቶችን ክትትልና እንክብካቤ ሚፈልጉ ነገሮች ላይ ይችሉበታል። »» በጎ አድራጎትና መደራጃ ማህበራት ላይም እንደዛው፣ ለምሳሌ ንግስት ዲያና( የዊሊያምና ሀሪ ልጅ) አንጀት ምትበለ ልዕልት እንደነበረች ማስታወስ እንችላለን፣ ጥሩ መካሪና ተከላካይ ናቸው። እንዴትና ምን ያህል ገንዘብ ተጠቅመው አንድን ስራ መጀመር እንዳለባቸው ያዎቃሉ፣ ሲኖራቸው ሁሌም ደስተኛ ናቸው፣ የሚሰሩትም ወይ ለዝና ወይ ደግሞ ራሳቸውን ለማሳወቅ አይደለም፣ ጀስት መስራት ስላለባቸው ነው። ከአላማቸውም ማንም አያዘናጋቸውም፣ ከሚፈልጉትም ነገር እንደዛው። √√ ጥሩ እሴቶች »» አሳቢ፣ ታጋዥ፣ ስሜታዊ፣ ፈጣሪ፣ ትጉ እንዲሁም ሰውን ማፅናናት ይችሉበታል። √√ ስኬታማ የስራ መስክ »» ሪል ስቴት፣ ዲዛይነር፣ ሳይኮሎጂስት፣ አስተማሪ፣ ቴራፒስት፣ ሁምን ሪሶርስ፣ የህግ ባለሞያ፣ ወታደር፣ CEO ፣ አማካሪ፣ ባንከር፣ ሼፍ፣ ፀሀፊ፣ አዋላጅ ፣ ፋርማሲስት፣ ሞግዚት፣ ባለ ስልጣንና የመሳሰሉትን ቢሆኑ የበለጠ ስኬታማ ይሆናሉ። √√ ተስማሚ ያልሆኑ መስኮች »» የተነጠለ ስራ ሆኖ ኦቨርሳይት ሚበዛበት ስራ።
የአኳሪየስ ተስማሚ የስራ መስክ Reviewed by nestamereja on 5:44 AM Rating: 5

No comments:

All Rights Reserved by NESTA MEREJA © 2014 - 2015
Powered By Blogger, Share by Star Tuan

please fill the following

Name

Email *

Message *

Theme images by konradlew. Powered by Blogger.