የቪርጎ ተስማሚ የስራ መስክ

የቪርጎ ተስማሚ የስራ መስክ The master, eagle eyed »» ቪርጎዎች እያንዳንዷን ነገር ጥንቅቅ ብለው ስለሚያዩ፣ ቴክኒካል ነገሮችን በደንብ የመስራት ብቃት አላቸው። ሚሰሩትንም ስራ ምርጥ አድርገው መስራት ይፈልጋሉ ምንም እንከን እንዲኖረው አይፈልጉም። ምርታማ ሰዎች ናቸው ማንም ማያየውንና ማይገነዘበውን ነገር ቁልጭ አድርገው ያያሉ። »» ስራ ላይ አንደኛና ጎበዝ ናቸው፣ መስራት ለነሱ ገንዘብ ማግኛ መንገድ ብቻ ሳይሆን የደስታና ከጭንቀት ነፃ መውጫ መንገዳቸውም ጭምር ነው። ሁሉንም ሰው ማያስጨንቀውን ነገር ያስጨንቃቸዋል፣ ለዚህም ነው እንከን እንደይገኝበት አድርገው ሚሰሩት። ለምሳሌ ደራሲዋን አጋታ ክርስቲን ብናያት፣ ጥንቅቅ ያሉና እንከን ማይገኝባቸውን የወንጀል ድርሰቶቿ ቃዋቂ አድርጓታል። »» ብዙ ነገሮችን ማስታወስ ይችላሉ፣ ፅዱና ጥንቁቅ ናቸው፣ ስለዚህም ከሌሎች ስራዎች ይልቅ የአግልግሎት(service) ሴክተር ላይ ቢሰማሩ የበለጠ ይሳካላችዋል፣ በዛ ላይ ሪሰርችና ስታቲክስን ቀለል አድርገው ማውጣት ይችሉበታል። ጫጫታና ውዥንብር የበዛባቸው ነገሮች ብዙም አይወዱም። √√ ጥሩ እሴቶች »» ጥቃቅን ነገሮችን ማስተካከል ላይ፣ ተንታኝ፣ ትጉ ፣ ስጉና ሚሰሩትንም ስራ በፕሮግራምና፣ እቅድ አውጥተው ነው። √√ ስኬታማ የስራ መስክ »» ኤዲተር፣ አካውንታንት፣ ኢንጂነሪንግ፣ ግራፊክስ ዲዛይነር፣ አበባ ሻጭ፣ ስታይሊስት፣ መርማሪ ፖሊስ፣ ዶ/ር፣ ነርስ፣ አስተማሪ፣ ተርጓሚና የመሳሰሉትን መሆን ይችላሉ። √√ ተስማሚ ያልሆኑ መስኮች »» ዝርክርክ ያለ የስራ ኢንቫይሮመንት ሆኖ ብዙ ሰዎች ሚበዙበትና፣ አልምጥ ሰራተኞች ያሉበት ማንኛውም ቦታ።
የቪርጎ ተስማሚ የስራ መስክ Reviewed by nestamereja on 5:45 AM Rating: 5

No comments:

All Rights Reserved by NESTA MEREJA © 2014 - 2015
Powered By Blogger, Share by Star Tuan

please fill the following

Name

Email *

Message *

Theme images by konradlew. Powered by Blogger.