የሊዮ ተስማሚ የስራ መስክ

የሊዮ ተስማሚ የስራ መስክ Follow the Leo, The star »» ሊዮዎች መስራት የሚፈልጉትን ነገር መስራት ይችላሉ፣ ብዙ ነገር ውስጥም ተሳትፎ ያደርጋሉ፣ ይሳካላቸዋልም። ግርማ ሞገሳም፣ አስተዋይ፣ ደፋር፣ እብድ፣ ፖዘቲፍ ኢነርጂና በመሪነትም ማንንም ማስገረም ይችላሉ፣ እስከሁን አለም ላይ ብዙዎቹ ፕሬስዳንቶችና መሪዎች ሊዮ ናቸው። በሀገራችንም እነ ዶ/ር አብይ አህመድና ኦቦ ለማ መገርሳን መየት እንችላለን። »» የሚሰሩትንም ስራ በአግባቡና አድሏዊ ባልሆነ መንገድ መስራት ነው የሚፈልጉት፣ ብዙ እቃዎችን ኦርደር በማድረግ፣ ፓርቲዎችን በመውደድና ዘና ማለትን ይወዳሉ፣ በተፈጥሯቸውም ሰው እንዲከተላቸው ማድረግ ይችላሉ፣ የሚሰሩትንም ስራ ያለምንም ተፅኖና ፍራቻ፣ በጥልቅ ተነሳሽነትና ወገንታዊነት ይሰራሉ፣ ሰማይ እንዳሉ ኮኮቦችም የሚፈልጉት ነገር ብዙ ነው፣ በሰሩት ስራም ምስጋናና ክብር እንዲሰጣቸው ይፈልጋሉ። ደፋር ቢሆኑም ውስጥ ውስጡን ፈራ ይላሉ። »» ተራ ሰራተኛ ወይም ከመጋረጃ ጀርባ የሚሰሩ ሰዎች አይደሉም፣ አይወዱምም፣ ካልሆነም ስራውን ለቀው ይሄዳሉ። ጭምቱም ሆነ ግልፁ ሊዮ፣ ቶሎ እንዲታወቁና እንዲደነቁ ይፈልጋሉ፣ ሁሉም ሊዮዎች የማዕረግ ስም ይወዳሉ፣ አመራር የመስጠት ፍለጎት በልባቸው ስር የሰደደ ነው ። √√ ጥሩ እሴቶች »» ኮንፊደንሳም፣ ተስፈኛ፣ ኢንተርፕሬነር፣ ደግና ሀይለኛ ናቸው፣ መስራት የሚፈልጉትም ስራ የእነሱን የተለያየ ብቃት የሚያሳይ ቢሆን ይመረጣል። እንዲሁም አስተዋፅዖ ማድረግ የሚችሉበትን። √√ ስኬታማ የስራ መስክ »» ኢንተርፕሬነር፣ ፕሬዝዳንት፣ ኢንተርቴይመንት፣ ፖለቲካ፣ ህዝብ ግንኙነት፣ ሴናተር ፣ ሙዚቀኛ፣ CEO ፣ አስተማሪ፣ አስጎብኚ፣ የሪልስቴት ባለቤት፣ ፋሽን ዲዛይነር፣ ሽያጭ፣ ሶሻል ሚዲያና የመሳሰሉት ላይ ምርጥ ናቸው። √√ ተስማሚ ያልሆኑ መስኮች »» ማንኛውም አይነት ስራ ይሁን፣ ጎልተው መውጣት የማያስችላቸው ከሆነ አይመቻቸውም።
የሊዮ ተስማሚ የስራ መስክ Reviewed by nestamereja on 5:34 AM Rating: 5

No comments:

All Rights Reserved by NESTA MEREJA © 2014 - 2015
Powered By Blogger, Share by Star Tuan

please fill the following

Name

Email *

Message *

Theme images by konradlew. Powered by Blogger.