አስቂኝ አባባሎች
ዶሮን ሲያታልሏት በሬ ነቃባቸው
ትክክለኛው አባባል :- ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት
ሁሉ አማረሽን ፌስ ቡክ ላይ አድ አድርጓት
ትክክለኛው አባባል :-ሁሉ አማረሽን ገበያ አታውጧት
ላም አለኝ በሰማይ አይሮፕላን ገጫት
ትክክለኛው አባባል :-ላም አለኝ በሰማይ ወተቷን የማላይ
የቆጡን አወርድ ብላ ብብቷ ታየባት
ትክክለኛው አባባል :-የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች
ተልባ ቢንጫጫ በፌደራል ይበተናል
ትክክለኛው አባባል :-ተልባ ቢንጫጫ በአንድ ሙቀጫ
ሲያዩት ያላማረ ፌስ ቡክ ላይ ያምራል
ትክክለኛው አባባል :-ሲያዩት ያላማረ ሲበሉት ያቅራል
ጅብ ከሄደ ለቀበሮ ያቃጥራል
ትክክለኛው አባባል :-ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ
ከፍትፍቱ አጉርሰኝ
ትክክለኛው አባባል :-ከፍትፍቱ ፊቱ
የነቶሎ ቶሎ ቤት ሰሞኑን ተመረቀ
ትክክለኛው አባባል :-የነቶሎ ቶሎ ግድግዳው ሰንበሌጥ
ጨው ለራስህ ብለህ ጣፍጥ ካለበለዚያ ባዶ እንበላለን
ትክክለኛው አባባል :-ጨው ለራስህ ብለህ ጣፍጥ ካለበለዚያ ድንጋይ ነህ ተብለህ ትጣላለህ
ሞኝና ወረቀት እኛ ሰፈር የለም
ትክክለኛው አባባል :-ሞኝና ወረቀት የያዘውን አይለቅም
በእጅ ያለ ወርቅ አንድ ቀን መሰረቁ አይቀርም
ትክክለኛው አባባል :-በእጅ ያለ ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል
ሴት ሲበዛ ቀላል አሪፍ ነው
ትክክለኛው አባባል :-ሴት ሲበዛ ጎመን ጠነዛ
አባይን ያላየ ሄዶ ማየት ይችላል
ትክክለኛው አባባል :-አባይን ያላየ የውሃ ምንጭ ያመሰግናል
ስራ ያጣ መነኩሴ ሪፖርተር ያነባል
ትክክለኛው አባባል :-ስራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል
አባይ ማደሪያ የለው አሁን ሊገደብ ነው
ትክክለኛው አባባል :-አባይ ማደሪያ የለው ግንድ ይዞ ይዞራል
ካለ ፈጣሪ አንሆንም ተጧሪ
ትክክለኛው አባባል :-ካለ ፈጣሪ አሟጠሽ ጋግሪ
የጅብ ችኩል በቀን ይወጣል
ትክክለኛው አባባል :-የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል
በሬ ከአራጁ ገንዘብ አይቀበልም
ትክክለኛው አባባል :-በሬ ከአራጁ ይውላል
በቅሎ ግዙ ግዙ ሳይወደድ
ትክክለኛው አባባል :-አንድ አሞሌ ጨው ላያግዙ
የምታቦካው የላት ሸማቾች ተሰለፈች
ትክክለኛው አባባል :-የምታቦካው የላት የምትጋግረው አማራት
የማያጠግብ እንጀራ እናቴ ጋገረች
ትክክለኛው አባባል :-የማያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል
ከኑግ የተገኘህ ሰሊጥ እዛው ተቀመጥ
ትክክለኛው አባባል :-ከኑግ የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ
ላም ባልዋለበት ተጠቆረ
ትክክለኛው አባባል :-ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ
ጊዜ የሰጠው ቅል ቡፌ ላይ ይቀመጣል
ትክክለኛው አባባል :-ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል
ላለፈው ክረምት አክስቴ ከውጭ መጣች
ትክክለኛው አባባል :-ላለፈው ክረምት ቤት አይሰራለትም
የፈሰሰ ውሀ አይታፈስም
ትክክለኛው አባባል :-የፈሰሰ ውሀ ካየ ውሃ ልማት ይቀጣል
የቄስ ሚስት አወቅሽ አወቅሽ ቢሏት ጥምጣም አስራ ላሳልም አለች
ትክክለኛው አባባል :-የቄስ ሚስት አወቅሽ አወቅሽ ቢሏት የባሏን መጽሀፍ አጥባ ቆየች
ያጣ ለማኝ ከጥቃቅን ይበደራል
ትክክለኛው አባባል :-ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል
እግረ ቀጭን ይሞታል ሲሉ እግሩ ወፈረ
ትክክለኛው አባባል :-እግረ ቀጭን ይሞታል ሲሉ እግረ ወፍራም ይቀድማል
ድሀ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ ኖሮ ቅቤ ይረክስ ነበር
ትክክለኛው አባባል :-ድሀ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ ኖሮ ንጣት ይገለው ነበር
ጌታዋን የተማመነች በግ ሶፋ ላይ ትቀመጣለች
ትክክለኛው አባባል :-ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን ውጭ ታሳድራለች
ጉልቻ ቢቀያየር ያው ለመሸከም ነው
ትክክለኛው አባባል :-ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም
ውሀ ሲወስድ እሳት ያቃጥላል
ትክክለኛው አባባል :-ውሀ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው
ሲሾም ያልበላ ሙሰኛ አይባልም
ትክክለኛው አባባል :-ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል
ዶሮ ብታልም አትስትም
ትክክለኛው አባባል :-ዶሮ ብታልም ጥሬዋን
አሳ ጎርጓሪ ስንጥብ ይወጋዋል
ትክክለኛው አባባል :-አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል
ገንዘብ ካለ የማያስቅ ያስቃል
ትክክለኛው አባባል :-ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ
የማያውቁት አገር በአይሮፕላን ይኬዳል
ትክክለኛው አባባል :-የማያውቁት አገር አይናፍቅም
ሰውን ማመን ቀብድ ተቀብሎ ነው
ትክክለኛው አባባል :-ሰውን ማመን ቀብሮ አለች ቀበሮ
እኔ ከሞትኩ የሚሸከምላችሁን ፈልጉ አለች አህያ
ትክክለኛው አባባል :-እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አለች አህያ
የሽሮ ድንፋታ ስጋ እስኪመጣ
ትክክለኛው አባባል :-የሽሮ ድንፋታ ከእሳት እስኪወጣ
የፉክክር ቤት ተሸጠ
ትክክለኛው አባባል :-የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል
ልጅ ለናቷ ታዘዘች
ትክክለኛው አባባል :-ልጅ ለናቷ ምጥ አስተማረች
ለተቀማጭ ወንበር አምጡለት
ትክክለኛው አባባል :-ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው
አንበሳ ሲያረጅ የተጣላ አንበሳን ይሸመግላል
ትክክለኛው አባባል :-አንበሳ ሲያረጅ የዝንብ መጫወቻ ይሆናል
ታሞ ከመማቀቅ ዶክተር ጋር መሄድ
ትክክለኛው አባባል :-ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ
የላጭን ልጅ ጸጉር ጠይቋት
ትክክለኛው አባባል :-የላጭን ልጅ ቅማል በላት
ከወፈሩ ሰው አይፈሩ
ትክክለኛው አባባል :-ከወፈሩ ሰው አይፈሩ
የአህያ ስጋ ሲሸጡ ተይዘው ታሰሩ
ትክክለኛው አባባል :-የአህያ ስጋ አልጋ ሲሉት መሬት
ልጅ ያቦካው ይበላላችኋል?
ትክክለኛው አባባል :-ልጅ ያቦካው ለራት አይበቃም
የደላው ከፎቅ ላይ ይዘላል
ትክክለኛው አባባል :-የደላው ሙቅ ያኝካል
ድሀ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ ኖሮ ቅቤ ባልተወደደ
ትክክለኛው አባባል :-ድሀ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ ኖሮ ንጣት ይገለው ነበር
ነገር በምሳሌ አንቦውሃ በጠርሙስ
ትክክለኛው አባባል :-ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ
ተንጋለው ቢተፉ ጣሪያውን ጭርት አስያዙት
ትክክለኛው አባባል :-ተንጋለው ቢተፉ ተመልሶ ከአፍ
ዞሮ ዞሮ ወደቤት ሲገባ ያደክማል
ትክክለኛው አባባል :-ዞሮ ዞሮ ወደቤት ኖሮ ኖሮ ወደ መሬት
የድሀ ቅንጡ በብድር ይደግሳል
ትክክለኛው አባባል :-የድሀ ቅንጡ እንጀራ ሲሰጡት ይላል ድልህ አምጡ
ጨው ለራስህ ታቅበታለህ
ትክክለኛው አባባል :-ጨው ለራስህ ብለህ ጣፍጥ
አንቺው ታመጪው አንችው ታጣዪው
ትክክለኛው አባባል :-አንቺው ታመጪው አንቺው ታሮጪው
የወጋ ቢረሳ የተወጋው ቲታኖስ ሆነበት
ትክክለኛው አባባል :-የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም
አያ ጅቦ አለህ ?
ትክክለኛው አባባል :-አያ ጅቦ ሳታመካኝ ብላኝ
የወደቀ ግንድ መሸጋገሪያ ሆነ
ትክክለኛው አባባል :-የወደቀ ግንድ ምሳር ይበዛበታል
ከዝንጀሮ ቆንጆ ተመርጦ ይሸለማል
ትክክለኛው አባባል :-ከዝንጀሮ ቆንጆ ምን ይመራርጡ
ሰውን ማመን ቀብድ ተቀብሎ
ትክክለኛው አባባል :-ሰውን ማመን ቀብሮ አለች ቀበሮ
ታሞ የተነሳ ወሬ አያስነሳ
ትክክለኛው አባባል :-ታሞ የተነሳ እግዜርን ረሳ
በቅሎን አባትሽ ማነው ቢሏት ይለፈኝ አለች
ትክክለኛው አባባል :-በቅሎን አባትሽ ማነው ቢሏት እናቴ ፈረስ ነች አለች
ዶሮ ብታልም ማን ይፈታላታል
ትክክለኛው አባባል :-ዶሮ ብታልም ጥሬዋን
የማያውቁት አገር ሄደው ቢያዩ ጥሩ ነው
ትክክለኛው አባባል :-የማያውቁት አገር አይናፍቅም
ውሀ ቢወቅጡት ሙቀጫው ታጠበ
ትክክለኛው አባባል :-ውሀ ቢወቅጡት እንቦጭ
አስቂኝ አባባሎች
Reviewed by nestamereja
on
3:09 AM
Rating:

No comments: