የኤሪስ ተስማሚ የስራ መስክ

የኤሪስ ተስማሚ የስራ መስክ The Trailblazer, authoritative »» ዞዳይክ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ኮኮቦች በጣም ሚሰማቸውን ነገር ብትጠይቋቸው። ኤሪስ መቼም ላላ ያለ ነገር እንደማይወዱ ይነግሯቸዋል። ኤሪሶች ሁሌም በሙሉ ሀይልና በፍክክር ሚሰራ ነገርን ይወዳሉ፣ ከሌሎችም ድፍረትና ጥንካሬ አላቸው። ዶ/ር አቴና እንደሚሉት ከሆነ ከፊታቸው የሆነ ግብ ተቀምጦ ካለ ግቡን በ200% በላይ እንደሚያሳኩት ተናግረዋል። »» የራሳቸውን ነገር መስራትና በትልቅ ቦታ በሀላፊነት መቀመጥ መፈለግ የኤሪሶች ባህሪ ነው። ለተፈጥሮ ነገሮች ርህራዬ አላቸው። ከማንም በላይ ተራማጅና እቅዶች ቢኖሯቸውም ብዙ ግዜ በደመ ነፍስ አንድ አንድ ስተቶች ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ። ንቁ ስለሆኑ ኮሚሽን ያለባቸው ስራዎች ላይ አሪፍ ናቸው፣ በተለይ ቦነስ ካለው የበለጠ ይሆናሉ። በድፍረታቸውና ቆራጥነታቸው የህይወት ዘመናችን ጀግኖች ያስብላቸዋል ። ምርጥ ኦፊሰርና፣ ጀግና ተዋጊ ወታደሮች ይዋጣላችዋል። »» ኤሪሶች ሀሳባዊ  ስራ ነው ሚፈልጉት፣ የሆነ ትንሽ ከበድ ሚል ስራ፣ ዝም ብሎ አይነት ሆኖ መደበርን አይፈልጉም፣ በማርስ የሚመሩት ኤሪሶች ሁሉኑም ነገር ሲጀምሩ፣ በሙሉ ልባቸው ነው። በውድድር ያምናሉ፣ ከግዜም ጋ ቢሆን መወዳደር ይፈልጋሉ። የራሳቸውንም ግዜ አጥብቀው ይፈልጋሉ። ሁሉንም በቅድመ ተከተል ስለማይሰሩ፣ የራሳቸው ነገር ቢኖራቸውና ቢሰሩ ይሻላቸዋል ። √√ ጥሩ እሴቶች »» ጉጉት፣ ትጋት፣ ፈጠራ፣ ልባዊ የሆነ ስራን ከኤሪስ ማግኘት ቀላል ነው።  ትላልቅ ነገር ላይ ምርጥ ነገሮችን ያሳያሉ ነገር ግን እያንዳንዱን ጥቃቅን ነገር ማውጣት አይወዱም። √√ ስኬታማ የስራ መስክ »» ጄኔራል፣ ኮማንደር፣ ኢንተርፕሬነር፣ ፊልምና ቴሌቪዥን፣ ሽያጭ፣ ስቶክ ሆልደር፣ የመንግስት ባለስልጣን፣ መዝናኛ ላይ፣ አትሌቲክስ፣ ዳንስ፣ አሰልጣኝ፣ አነቃቂ ንግግሮች ላይ፣ CEO፣ ኢንጂነሪንግና የመሳሰሉት ለይ ምርጥ ናቸው። √√ ተስማሚ ያልሆኑ መስኮች »» ተራ የተለመዱና፣ እያንዳንዱን ጥቃቅን ነገሮች መስራት ያለበት ስራ አይነት አይሆንላቸውም።
የኤሪስ ተስማሚ የስራ መስክ Reviewed by nestamereja on 5:03 AM Rating: 5

No comments:

All Rights Reserved by NESTA MEREJA © 2014 - 2015
Powered By Blogger, Share by Star Tuan

please fill the following

Name

Email *

Message *

Theme images by konradlew. Powered by Blogger.