how to know faka and orginal samsung smartphone in amharic

 ሳምሰንግ ስልኮች ተፈላጊነታቸዉ እየጨመረ በመጣ
ሳምሰንግ ከኦርጂናሉ ጋር ተመሳስለዉ በቻይና የሚመረቱ
ፌክ ሳምሰንግ ስልኮችም በዛዉ መጠን ይጨምራሉ፡፡
ሳምሰንግ የጉግልን አንድሮይድ ኦፐሬቲንግ ሲስተም
ይጠቃማል፣የአንድሮይድ ሲስተም ኮድ ደግሞ ማንኛዉም
ፍላጎት ያለዉ አካል ኮዱን እንዲጠቀም የሚያስችል ፍቃድ
ስለሚሰጥ፣ አጭበርባሪ ድርጅቶች ከኦርጂናሉ ስልክ
ከፍተኛ ቅናሽ ያለዉን ተመሳሳይ ፌክ ሳምሰንግ ስልክ
በማምረት ገበያዉን ያጥለቀልቁታል፡፡
ኦርጂናሉን ስልክ ከፌኩ በቀላሉ መለየት ያስቸግራል፣
ነገር ግን እነዚህን መንገዶች በመጠቀም ፌክ ሳምሰንግ
ስልኮችን መለየት ይችላሉ;
፩.የስልኩን ቀፎ አካላዊ ገጽታዎች በመገምገም 
ፌክ ሳምሰንግ ስልክ፡
1) የስክሪኑ መስታወት ጥራት የለዉም
2) ስክሪኑ ከቀፎዉ ጠርዝ በጣም ይርቃል
3) ስክሪኑ ድምቀት ይጎድለዋል
4) የሳምሰንግ ሎጎ(ሳምሰንግ የሚለዉ ጽሁፍ) ሲነካ
ይሻክራል፣በደንብ ከተጫኑት ይለቃል
5) ከኦርጂናል ስልኮች ጋር ሲያስተያዩት፤ ባትሪዉ
መክደኛዉን ሲከፍቱ የሚታዩ ትንንሽ አካሎች እና ባትሪዉ
ላይ የሚገኙት መረጃዎች የተለያዩ መሆናቸዉን
ይመለከታሉ፡፡
፪.የስልኩን ፍጥነት እና የትእዞች አፈጻፀም በመገምገም
1) በስልኩ ፎቶዎችን ለማንሳት ይሞክሩ፣በፌክ ሳምሰንግ
ስልኮች የሚያነሱት ፎቶ ጥራት የወረደ ስልኮች
2) በተመሳሳይ ጊዜ በርካታ ጌሞች እና አፕሊኬሽኖችን
ለመክፈት ይሞክሩ፣ፌክ ስልኮች ስታክ(ቀጥ) የማለት
ባህሪይ ያሳያሉ፡፡
3) ስልኩን አጥፍተዉ ያብሩት፣ ፌክ ስልኮች ቶሎ ባህሪይቱም
፫.የስልኩን የምርት መረጃዎች በመገምገም 
1) ወደ ዋናዉ ማዉጫ ይሂዱ እና አፕስ(Apps)
የሚለዉን ቁልፍ ይጫኑ
2) ከአፕሊኬሽን ማዉጫዉ ላይ፣ Settings የሚለዉን
ይጫኑ
3) ከ Settings ላይ More የሚለዉን ይጫኑ እና
Storage የሚለዉን በመጫን ስልኩ ላይ መጫን
ሚችሉትን የዳታ መጠን ይመልከቱ፤ ከኦርጂናሎቹ ስልኮች
በጣም ያነሰ ከሆነ ፌክ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡
4) እንዲሁም About device የሚለዉን ይጫኑ እና
የስልኩን ሞዴል ቁጥር እና baseband, build number
ጉግል ላይ ይፈልጉት፣ የሚያገኙት መልስ ተጠቀሱትን
ኦርጅናል መሆኑን ይነግሮታል፡፡
፬. የሳምሰንግ ኮዶችን በመጠቀም 
ወደ ስልክ መደወያዉ በመሄድ፣ከዚህ በታች የተጠቀሱትን
ኮዶች ያስገቡ እና Call የሚለዉን ወደኑ፤ ስልኩ
ያስገቡትን ኮድ አዉቆ መልስ መስጠት ከቻለ ኦርጅናል
መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡ ካልሆነ ግን ፌክ ስልክ ነዉ፡፡
1) #0# - አጠቃላይ መገምገሚያ
2) #1234# or #9999# - ስልኩ የሚጠቀመዉን
ሶፍትዌር እና ሞደም ማወቂያ
3) #12580369# - ስለ ስልኩ ሶፍትዌር እና ሀርድዌር
ማወቂያ
4) #06# - የስልኩን ኢንተርናሽናል መለያ ቁጥር
ማወቂያ
5) #9998246# - የስልኩን የባትሪ እና ሚሞሪ
መረጃዎች ማወቂያ
፭. ሳምሰንግ ኪይስ(Samsung Kies) ሶፍትዌርን
በመጠቀም *
ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች ፌክ ሳምሰንግ ስልክን መለየት
ካልቻሉ ይህን ሶፍትዌር ይጠቀሙት፡፡
1) Samsung Kies ሶፍትዌርን ኮምፒዉተሮት ላይ ይጫኑት
 የፈለጉትን ስልክ ከኮምፒዉተሮት ጋር
ያገኛኙት
3) ሶፍትዌሩ ስልኩን ያነበዉ እና የስልኩን ስም
፣የሚጠቀመዉን ሶፍትዌር እና ሀርድዌር ያሳያል፤ ሶፍትዌሩ
ስልኩን ማንበብ ካልቻለ በድጋሚ ይሞክሩት በድጋሚ
ማንበብ ካልቻለ ሰልኩ ፌክ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡
how to know faka and orginal samsung smartphone in amharic Reviewed by nestamereja on 10:35 PM Rating: 5

No comments:

All Rights Reserved by NESTA MEREJA © 2014 - 2015
Powered By Blogger, Share by Star Tuan

please fill the following

Name

Email *

Message *

Theme images by konradlew. Powered by Blogger.