ስለ ጌዜ about time


"ጊዜ የዘላለም አሽከር ሲሆን፣ ሰው ደግሞ የጊዜ ባሪያ ነው።ሰው ጊዜን በደቂቃና በሰአት፣ በወራትና በዓመታት ሸንሽኖ፣ ከግድግዳው ላይ ሰቅሎ በእጁ ላይ ጠፍሮ ሊገዛው ሊቆጣጠረው ይሞክራል። ጊዜ ደግሞ ሰውን ከልጅነት ወደ ወጣትነት ከጉልምስና ወደ እርጅና  እያክለፈለፈ ከሞት ደጃፍ ያደርስና መቃብር ይጨምረዋል። በክረምትና በበጋ ፣በጸደይና በመጸው እየተመሰለ መልኩን እየቀየረ ሲመጣና ሲሄድ ሲዞርና ሲፈራረቅ፣.... የጊዜ ጉዞ ያዙሪት እንጂ የወደፊት አይመስልም። በድል ፈረስ ላይ ተቆናጦ በስኬትና በውድቀት፣ በቀጠሮና በድንገት በጥበቃ እና በጥድፊያ ተጠቅሞ የሰውን እጣፈንታ የሚወስን ጊዜ መሆኑን በቀላሉ እንዘነጋለን። ጊዜን መግዛት ሲባል ራስን እንጂ ጊዜን ማስገዛት አይደለም።


    "በጊዜ ውስጥ ትናንት የትዝታ ፣ነገ ደግሞ የተስፋ ጎተራ ናቸው። ካመለጠ ትናንት....ያልመጣ ነገ ይሻላል። በእጅ ያለ ዛሬ ግን ከሁሉም ይበልጣል። ዛሬ ሁሌም ያለ እየመሰለ የማይደገም... ተመልሶ የማይመጣ .....ላንድ አፍታ ለቅፅበት ታይቶ ዳርቻ ከሌለው የዘላለም ጠፈር ገብቶ የሚሰወር... በትናንትናና በነገ መሃል የተሰነቋረ እንቁ ነው። የዛሬ ሚስጢሩ ና ጉልበቱ ያለው ደግሞ "አሁን" ነው። "ቅድም" እና "በኃላ" ግን ያለ ቦታቸው ዛሬ ውስጥ የተደነቀሩ የትናንትናና የነገ ሽርፍራፊዎች ናቸው።
➷👉ምንጭ 📖 ሌላ ሰው (ዶ/ር ምህረት ደበበ
 ◎●●◉◉JOIN on telegram ◉◉●●◎
https://t.me/dishwork_348
♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥
ስለ ጌዜ about time Reviewed by nestamereja on 12:17 AM Rating: 5

No comments:

All Rights Reserved by NESTA MEREJA © 2014 - 2015
Powered By Blogger, Share by Star Tuan

please fill the following

Name

Email *

Message *

Theme images by konradlew. Powered by Blogger.