የአለቃ ገብርሃና ቀልዶች funny aleka gebirhana
እኔ ለነካሁት
አለቃ እንዲሁ ሴት ጋር ያድሩና ጠዋት ቤተክርስቲያን ሲሄዱ ይከለከላሉ እንዳይገቡ ያያቸው ሰው ስለነበር። እናማ በሴቶች በር በኩል ሄደው ዛሬ ሴቶች አይገቡም እዚህ ከገርገራው ውጪ ሆናችሁ ጸልዩ ብለው ሴቱን ሁሉ ከልክለው ካህናቱ ገርሟቸዋል አንድም ሴት ሳያዩ በመቅረታቸው። «ምን ሆነው ነው?» ሲሉ አንድ ያለቃን ስራ ያየ ካህን «አለቃ ከልክለው ነው ሴቶች እንዳይገቡ» ብሎ ያስረዳል።አለቃም ተጠርተው ሲጠየቁ «እኔ ለነካሁት ከተከለከልኩ እነሱ ይዘው እንዴት ይግቡ» ብዬ ነው አሉ።
መውጫችንን ነዋ
ቦታው የት እንደሆነ አላውቅም ብቻ ጣይቱ በእንጨት ደረጃ ወደ ፎቅ ይወጣሉ። ድሮ ያው ግልገል ሱሪ አልነበረም ፎቅ ሲወጡ አለቃ ደረጃው ስር ሆነው አንጋጥጠው የጣይቱን ምስጢር ያያሉ። ጣይቱም መለስ ብለው ወደታች ወደ አለቃ አዩና አለቃ «ምን እያዩ ነው?» ቢሏቸው። «መውጫችንን ነዋ» አሏቸው።
ኩኩሉ
መኳንንቱ በአለቃ ፍጥነት የሰላ አቃቂር ምን እናድርግ ብለው መከሩ። ነገ ሁላችንም እንቁላል ይዘን እንምጣና አለቃን እናፋጣቸው ብለው ተስማምተው በማግስቱ ጉባኤ ሁሉም ከኪሱ እንቁላሉን ብቅ ሲያደርግ አለቃም በቅጽበት እጃቸውን አርገፈገፉና ኩኩሉ አሉ። ከዚያም ለጥቀው ይህንን ሁሉ እንቁላል ያስወለድኩት እኔ ነኝ አሉ ይባላል። መኳንንቱ ሁሉ ሴት ዶሮ ሆነ።
በጠማማ ጣሳ
በአለቃ ተረብ በተደጋጋሚ ጥቃት ደርሶበት በቁጭት ላይ የነበረ ሰው እርሳቸውን የሚተርብበት ጥሩ አጋጣሚ በማግኘቱ እጅግ በጣም ደስ ይለዋል። ይሄውም አለቃ እሰው ቤት እንጀራ በምስር ወጥ ተጋብዘው እስኪጠግቡ ይበሉና በወጡ የተለቃለቀውን አፋቸውንም ሆነ ከንፈራቸውን ሳይታጠቡ ሰው ወደተሰበሰበበት አደባባይ ይመጣሉ። ሰውዬውም ያገኘውን አጋጣሚ በመጠቀም በሰው ፊት አዋርዷቸው ዝና ሊያገኝ በመጣደፍ፤ «አለቃ! በዛሬው ገበያ የምስር ዋጋ ምን ያህል ነበር?» ይላቸዋል። አለቃም የሰውየውን ተረብ በቅጽበት ይረዱና ቀና ብለው ሰውየውን ሲያዩት ጉንጩ በጣም የከሳና የተጣመመ መምሰሉን ይረዳሉ። ታዲያ ለሰውየው የሚሰጡት መልስ ምን መሰላችሁ። «አይ ልጄ! ምስርማ ዛሬ ተወዶ በጠማማ ጣሳ በብር አንድ ሲሸጥ ውሏል።» በማለት የጉንጩን መጣመም ጠቆም አድርገው ቆሽጡን አሳረሩት ይባላል።
አስደግፈውት አመለጡ
አለቃ መቼም ሲናገሩ ለነገ የለም እና አንዱን ዲያቆን አበሳጭተውት ሊደበድባቸው ይፈልጋቸዋል።እናም አንድ እለት በሩቅ ያዩትና ሮጠው እንደማያመልጡት ሲገባቸው ቶሎ ሮጥ ብለው አንድ ዘመም ወዳለ ጎጆ ይሄዱና ሊወድቅ ያለውን የጎጆውን ግድግዳ በጃቸው ደግፈው እንደቆሙ፤ ዲያቆኑ ይደርስባቸውና ምን እያደረጉ እንደሆነ ይጠይቃቸዋል። እሳቸውም ግድግዳው ሊወድቅ ስለሆነ ደግፈው መቆማቸውን እና እሱ ቢተካላቸው አጣና አምጥተው ግድግዳውን እንደሚያስደግፉ ነግረውት እሱ ሲተካላቸው አለቃ አስደግፈውት አመለጡዋ። አይ የያዛቸው ቀን እኔ የለሁበትም ቆርጦ ቆርጦ ነው የሚጥላቸው።
በሰው አገር ቀረሁ
አለቃ መንገድ ወጥተው ይመሽባቸውና የመሸበት እንግዳ ብለው ሰው ቤት ይጠጋሉ። በኋላም ያረፉባት ሴትዮ ያለቃን ተረብ ታውቅ ኖሮ ተጨንቃ ተጠባ አሳ ወጥ ሰርታ እራት ታቀርባለች። ያው ሴትየዋም አሳው ወጥ ላይ የማይገባበትን ውሀ ጨምራበት ነበርና ትንሽ ቀጠን ብሎ ነበር። ታዲያ አለቃም የቀርበላቸውን እራት ጥርግ አድርገው ከበሉ በኋላ ለቅሶ ይጀምራሉ። እንደው ያዙኝ ልቀቁኝ ሰዎቹም ተጨንቀው አረ አለቃ ምነካዎ? ብለው ቢጠይቁ «አዬ አሳ አገሩ ሲገባ እኔ በሰው አገር ቀረሁ» ብለው የሴትየዋን የአሳ ወጥ በደንብ አለመስራት ተናገሩ።
ከአልጋ ላይ ወድቄ ነው
አለቃ አንድ ቀን መንገድ መሽቶባቸው አንዲት ሴትዮ ቤት እንድታሳድራቸው ለምነው ቤት ለእንግዳ ብላ አስገባቻቸው። አለቃ ያው እንደሚተረከው ቅንዝራም ቢጤ ናቸው። እራት በልተው ከጨረሱ በኋላ በሉ እኔ መደብ ላይ እርሶ መሬት ላይ ተኙ ብላቸው ተኙ። ከዚያ ጨለማን ተገን በማድረግ ሴትየዋ መደብ ላይ ዘፍ ብላው መዳሰስ ይጀምራሉ። ሴትየዋም በድንጋጤ ነቅታ እንዴ ምን እየሰሩ ነው ስትላቸው ከአልጋ ላይ ወድቄ ነው አሏት። እንዴት መሬት ተኝተው ስትላቸው እኔንስ የገረመኝ እሱ አይደል አሏት ይባላል።
የተልባ ማሻው ሚካኤል
አለቃ ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር ሲመለሱ ያው የግድ የአባይን በረሀ ማቋረጥ ነበረባቸው። አብረዋቸው የነበሩ መንገደኞች በቃ የአባይ ሽፍታ ሊዘርፈን ነው ብለው ሲያለቃቅሱ። አለቃ ብራችሁን ሰብስቡና አምጡ ብለው – መንገድ ሲሄዱ ተልባ እየወቀጡ የሚበሉበት ሙቀጫ ውስጥ ብሩን በሙሉ ይጨምሩና አፉን ወትፈው፤ ሙቀጫውን የቤተ ክርስቲያን ጨርቅ አልብሰው ለአንዱ መንገደኛ እንደታቦት አሽክመው ሲጓዙ ሽፍቶቹ ዘንድ ይደርሳሉ። ሽፍቶቹም ብቅ ብቅ ይሉና «ምንድናችሁ?» ይላሉ። አለቃም ፈጠን ብለው «ታቦት ልናስገባ ይዘን የምንመጣ መንገደኞች ነን» ይላሉ። አንዱ ሽፍታም «የታቦቱ ስም ማን ነው?» ይላል። አለቃም «የተልባ ማሻው ሚካኤል ነው» ብለው መለሱ። ሽፍቶቹም ተሳልመው መንገደኞቹም በሰላም በረሀውን አለፉ።
ወላሂ ኑ እንብላ
አለቃ ከሩቅ ቦታ ወደ አገራቸው ሲመለሱ ሽፍቶች ሊደርሱባቸው ሲል ያላቸውን ገንዘብ አገልግል ውስጥ ከተው ጠበቁዋቸው። ለሽፍቶቹም ኑ እንብላ ወላሂ ጥሩ የዶሮ ወጥ ነው ቢሏቸው እኛ የእስላም ስጋ አንበላም ብለው ትተዋቸው ሔዱ ይባላል።
ግም ግም ሲል
ሊቁ ገብረሀና በሀያ ስድስት ዓመታቸው ጎንደር ውስጥ ሊቀ ካህናት ሆነው ተሾሙ። በዚህ ጊዜ አንዲት ጎንደሬ ዘንድ ጠበል ተጠርተው ቢሄዱ የሚወጡት ሰዎች ሁሉ «ጠላው ጥሩ አይደለም» ሲሉ ይሰሙና ተመልሰው ወደቤታቸው ይሄዳሉ። ሴትዮዋም በመቅረታቸው አዝና ቤታቸው ሄዳ «ምነው አባ ጠበል ጠርቼዎት ሳይመጡ ቀሩ?» ብትላቸው “ኧረ መጥቼ ሰው ግም ግም ሲል ጊዜ ነው የተመለስኩት።” አሏት።
ቢሻን እንበላለን ቢሻን እንጠጣለን
በሀገራችን እንደተለመደው ድግስ ካለ ቄሱም ሼሁም ሁሉም እንደየሀይማኖቱ ይጠራሉ። አዝማሪዎችም አይቀሩም። ስለዚህ የአለቃ ግዳጅ አንዱ ድግስ መሄድ ነው። ሴትየዋ ያው እንደነገሩ አሸር ባሸር የሆነ ድግስ ብጤ አድርጋ ኖሮ አለቃ ወጡም ቅጥንጥን ጠላውም ውሀ ውሀ ብሎባቸው ኖሯል። ደጋሽ መጥታ አለቃ ይብሉ እንጂ ትላለች። አለቃም «የመጣንበትን ቢሻን እንበላለን ቢሻን እንጠጣለን» ብለው የልባቸውን ተናገሩዋ ድግሱን የፈቀዱ መስለው።
ከመሶብዎ አይጡ
ሰው መቼም ወዶም ይሁን ፈርቶ አለቃን ይጋብዛቸዋል። አንድ ቀን ሊጋበዙ ወደ አንዱ ቤት ጎራ ብለው እንደተቀመጡ ጋባዥዋ ሴት እንጀራ ለማቅረብ መሶቡን ከፈት ስታደርገው ትንሽ አይጥ ዘላ ትወጣና ትሰወራለች። አለቃም ይህችን ጠንቀኛ አይጥ አይተዋት እንዳላዩ ጸጥ ብለዋል። ርቧቸው ስለነበረ ከራሳቸው ጋር እየታገሉ እስኪበቃቸው ድረስ ይበላሉ። ከዚያም በመጨረሻ ማእድ ሲነሳ መመረቅ የተለመደ በመሆኑ እንዲህ ብለው ይመርቃሉ ;- በላነው ጠጣነው ከእንጀራ ከወጡ እ /ር ይስጥልኝ ከመሶብዎ አይጡ።
የመጣሁበት ነው
አለቃ ገብረሀና አንድ ጣና ሀይቅ ላይ ካለ ደሴት ላይ የምትኖር ሴት ጸበል ቅመሱ ብላ ትጠራቸዋለች። አለቃም በጥሪው ቀን በጀልባ ተሳፍረው ከጥሪው ቦታ ይደርሳሉ። ነገር ግን ትንሽ አርፍደው ነበርና ብዙው ምግብ ቀድሞ በመጣው ተጋባዥ ተበልቶ ወደማለቁ በመቃረቡ ያለውን ወጥ እንደ ነገሩ
የአለቃ ገብርሃና ቀልዶች funny aleka gebirhana
Reviewed by nestamereja
on
12:14 AM
Rating:
No comments: