የስኮርፒዮ ተስማሚ የስራ መስክ

የስኮርፒዮ ተስማሚ የስራ መስክ the soulful, midheaven »» ስኮርፒዮዎች ሁሉንም ነገር በጥልቅና እውቀት በተሞላበት ነገር መጠን ማወቅ ይፈልጋሉ፣ ነገሮችንም አስፍተው ነው የሚያዩት፣ የሰዎችን ችግር መረዳትና ድጋፍ ማደረግ ላይም ጎበዝ ናቸው፣ በዚህም ቋሚ ተማኝነትና የረጅም ግዜ ጓደኝነትን ይፈጥራሉ። ዶ/ር ፓራኪሶ እንደሚሉት ከሆነ ፣ ስኮርፒዮዎች የቴራፒስት እውቀት ስላላቸው የሰውን የውስጥ ችግር መረዳት እንደሚችሉም ይናገራሉ። »» በዛ ላይ የሌሎችን ሚስጥር መጠበቅ ላይ ጎበዝ ናቸው፣ እንደው በአጠቃላይ ስኮዎች ምን አይነት ስራ የሚወዱ ይመስላቹዋል? በቦንብ የቆሰለን ሰው የሚረዱ? ወይስ ውስብስብ ቀዶ ጥገናዎችን በስኬት የሚያደርጉ? እመኑኝ ስኮዎች በየትኛውም የስራ ዘርፍ ላይ ቢሆን ትፈልጓቸዋላቹ፣ እስከ ጥግ ትኩረት አድርጎ መስራትን ያውቁበታል። »» ነገር ግን አጠገባቸው አታንዣቡ፣ ነፃነትንና የሰራተኞቻቸውን እምነት ይፈልጋሉ፣ ግለኝነታቸውም እንዲጠበቅላቸው ይፈልጋሉ፣ ይሄ ማለት ከእነሱ ፍቃድ ውጪ ማንም ሰው ስራቸውን ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ አይፈልጉም። √√ ጥሩ እሴቶች »» ታታሪ፣ የፈጠራ ችሎታ ያላቸው፣ እምቅ ብቃትና ቆራጥነት፣ እንዲሁም ብዙ ግዜ ሰውን ሳይጠብቁ ይሰራሉ። ነገር ግን በጣም የሚጓጓለት ነገር ቢሆን ይመርጣሉ። √√ ስኬታማ የስራ መስክ »» ሳይኮሎጂስት፣ ህግ አዋቂ፣ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሰራተኛ፣ መርማሪ ፖሊስ፣ አስተማሪ፣ ሳይንቲስት፣ ሳርጂዮን፣ ፊዚስት፣ ፖሎቲከኛ፣ ፀሐፊ፣ ቴራፒስት፣ ዶክተርና እንዲሁም አስትሮሎጂና አንድ አንድ ጥበባት ላይ ጎበዝ ናቸው። √√ ተስማሚ ያልሆኑ መስኮች »» ትልቅ እውቀት ሳይኖራቸው የሚሰሩት ስራና ሳያምኑበት የሚገቡበትን ነገር መስራት ስኬታማ አያደርጋቸውም።
የስኮርፒዮ ተስማሚ የስራ መስክ Reviewed by nestamereja on 5:38 AM Rating: 5

No comments:

All Rights Reserved by NESTA MEREJA © 2014 - 2015
Powered By Blogger, Share by Star Tuan

please fill the following

Name

Email *

Message *

Theme images by konradlew. Powered by Blogger.